ስለ ማህበሩ
የማህበሩ እራይ
መቄዶንያ የአረጋዊያንና አእምሮ ህሙማን መርጃ ማህበር ሀገር ኢትዮጵያ ሁሉም አረጋዊያንና የአካል ጉዳተኞች መሰረታዊ ለሆኑ የሕይወት ፍላጎቶቻቸው ተደራሽነት ሆኖ የሚታዩበት ሀገር ሆና
የማየት እራይ ሰንቆ ይንቀሳቀሳል፡፡
ተልዕኳችን
ይህ ማኅበር ጧሪ ቀባሪ ለሌላቸው አረጋዊያንና ለአእምሮ ህሙማን የሚያስፈልጉትን መጠለያ፣ አልባሳት፣ ምግብና ሰባዊ እንክብካቤ ለመስጠት ቆርጦ የተነሳ ድርጅት ነው፡፡ ቅድሚያ የሚስጣቸውን የእነዚን ሰዎች መሀበራዊ ጉዮች ለማሳካትና አስፈላጊዉን ድጋፍ ለማድረግ የተለያ መንገዶችና ስልቶችን ይጠቀማል፡፡
የማህበሩ ግብ (ዓላማ)
የማህበሩ ግብ (ዓላማ) አረጋዊያንና የአካል ጉዳተኞች የተመቻቸ ኑሮ እንዲኖሩ ማስቻል ነው፡፡
ዝርዝር ዓላማዎች
1. ርህራሄ
2. ሁሉን ማካተት
3. ሁሉንም ማክበር
መቄዶንያ የአረጋዊያንና አእምሮ ህሙማን መርጃ ማህበር ሀገር በቀል፣ መንግስታዊ ያልሆነ፣ ለትርፍ ያልተቋቀቋመ እና ነፃ ሆኖ የሚሰራ ግብረ ሰናይ ድርጅት ሲሆን የተመሰረተዉም በታህሳስ 2002 ዓ.ም ነው፡፡ የማህበሩ ዓላማ አረጋዊያንን፣ የአካል ጉዳተኞችንና በህይወት ለመኖር ምንም ዓይነት አማራጭ የሌላቸውን ሰዎች መርዳት ሲሆን ይህንም የሚያደርገው መጠለያ፣ ልብስ፣ ምግብና ሌሎች መሠረታዊ የሆኑ ነገሮችን በማቅረብ ነው፡፡ ይህ ማህበር መቀመጫዉን ኢትዮጵያ ውስጥ ያደረገ ግብረ ሰናይ ድርጅት ሲሆን ዋና መቀመጫውን በኢትዮጵያ አዲ አበባ ባደረገው የኢትዮጵያ ፍደራላዊ መንግስት ግብረ ሰናይ ድርጅቶችና ማሕበራት ኤጀንሲ መተዳደሪያ ህግ ስር ያለ ሕጋዊ አካል ነው፡፡ ባሁኑ ጊዜ መቄዶንያ የአረጋዊያንና አእምሮ ህሙማን መርጃ ማህበር ከላይ የተጠቀሱትን አገልግሎቶች 70 (ሰባ) ለሚሆኑ የአእምሮ ህሙማንና መጠጊያ ለሌላቸው አረጋዉያን እየሰጠ ይገኛል፡፡እንኚህ ሰዎች መኖሪያ ቤት አልባ የነበሩ ሲሆን እንደ ሀዋሳ፣ ደብረዘይት፣ ደብረሊባኖስ፣ አዲስ አበባና ጉደር ከመሳሰሉ የተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የተሰባሰቡ ናቸው፡፡ ብዙዎቹ ሰዎችን የሰውነትና ፀጉርና፣ የእንቅስቃሴ፣ የሽንትቤት አጠቃቀም፣ የልብስ አለባበስና የጥርስ ንፅህና እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ናቸው፡፡
ይህ ማህበር አገልግሎቱ ተጠቃሚ ላልሆኑት ተደራሽነት እንዲኖረው በማሰብ ሁለገብ የሆነ ሕንፃ ለመገንባት በማቀድ ላይ ይገኛል፡፡ መቄዶንያ የአረጋዊያንና አእምሮ ህሙማን መርጃ ማህበር
የአረጋውያንን እና የአዕምሮ ህሙማንን ፍላጎት ለማመሟላት ከፍተኛ ጥረትን የሚያደርግ ድርጅት ነው!
ይህ ማህበር አገልግሎቱ ተጠቃሚ ላልሆኑት ተደራሽነት እንዲኖረው በማሰብ ሁለገብ የሆነ ሕንፃ ለመገንባት በማቀድ ላይ ይገኛል፡፡ መቄዶንያ የአረጋዊያንና አእምሮ ህሙማን መርጃ ማህበር
የአረጋውያንን እና የአዕምሮ ህሙማንን ፍላጎት ለማመሟላት ከፍተኛ ጥረትን የሚያደርግ ድርጅት ነው!
የማህበሩ እራይ
መቄዶንያ የአረጋዊያንና አእምሮ ህሙማን መርጃ ማህበር ሀገር ኢትዮጵያ ሁሉም አረጋዊያንና የአካል ጉዳተኞች መሰረታዊ ለሆኑ የሕይወት ፍላጎቶቻቸው ተደራሽነት ሆኖ የሚታዩበት ሀገር ሆና
የማየት እራይ ሰንቆ ይንቀሳቀሳል፡፡
ተልዕኳችን
ይህ ማኅበር ጧሪ ቀባሪ ለሌላቸው አረጋዊያንና ለአእምሮ ህሙማን የሚያስፈልጉትን መጠለያ፣ አልባሳት፣ ምግብና ሰባዊ እንክብካቤ ለመስጠት ቆርጦ የተነሳ ድርጅት ነው፡፡ ቅድሚያ የሚስጣቸውን የእነዚን ሰዎች መሀበራዊ ጉዮች ለማሳካትና አስፈላጊዉን ድጋፍ ለማድረግ የተለያ መንገዶችና ስልቶችን ይጠቀማል፡፡
የማህበሩ ግብ (ዓላማ)
የማህበሩ ግብ (ዓላማ) አረጋዊያንና የአካል ጉዳተኞች የተመቻቸ ኑሮ እንዲኖሩ ማስቻል ነው፡፡
ዝርዝር ዓላማዎች
- በማህበሩ ሥር ለታቀፉ አካል ጉተኞችና ድጋፍ የሌላቸው አረጋዊያን የሚያስፈልጓቸው መሠረታዊ አገልግሎቶች መስጠት፡፡
- ለአካል ጉዳተኞችና ድጋፍ ለሌላቸው አረጋዊያን ርዳታ በማድረግ የራሳቸው የሆነ ሥራ መሥራትየሚያስችላቸውን አቅም ማሳደግና በማህበረሰቡ የእለት ከለት እቅስቃሴ ውስጥ በሙሉ አቅም እንዲሳተፉ ማስቻል፡፡
- ድህነትን ለመቀነስ ለሚረገው ጥረት የበኩልን አስተዋፅኦ ለማድረግ መንግስታዊ ከሆኑ ተቋማት፣ ከሙያ ማህበራትና ከሌሎች ተቋማት ጋር የመረጃ ልውውጥን፣ ወዳጅነትንና የልምድ ልውውጥን ማሳደግ፡፡
- የአካል ጉተኞችና አረጋዊያን ለማህበራዊ ግልጋሎቶች ያላቸውን
- በአካል ጉዳተኛ ሰዎችና በአረጋዊያን ላይ ጥናት ማድረግና ውጤቱን ለዉይይት ማቅረብ፡፡
- አካል ጉዳተኞች ያላቸውን አካላዊና አእምሮአዊ ብቃት እንዲያዳብሩ ማበረታታት፡፡
- የአካል ጉተኞችንና ድጋፍ የሌላቸውን አረጋዊያን ብቃቶች፣ ፍላጎቶች፣ችግሮች፤ በሕዝቡ እንዲታወቁና ተቀባይነት እንዲኖራቸው ማድረግ ፡፡
- የአካል ጉዳተኞችንና አረጋዊያንን ብቃት መልሶ መቋቋምና የሥራ እድሎችን ማሻሻል፡፡
- የተቀናጀና ሁሉን አቀፍ የሆነ የማሕበረሰብ እድገት ለማምጣት መስራት፤ በተለይም የፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶች ማብቃት እና ራሳቸውን ማስቻል
1. ርህራሄ
2. ሁሉን ማካተት
3. ሁሉንም ማክበር
ድርጅቱን የምንደግፍባቸው መንገዶች ይህ ሶስት ነገሮችን ያጠቃልላል፡፡
1. ጊዜ
- ቀላል የሆነ ጉብኝት (ጥያቄ) ማድረግ
- ተስማሚ ቃላትን በመጠቀም አረጋዊያኑን ማነጋገር
- ሃሳባቸውን እንዲያካፍሉን ማድረግ
2. ተሰጥኦ (ችሎታ)
- እውቀትንና ልምድን ማካፈል
- ለተጠቃሚዎች ሰብአዊ እንክብካቤ፣ የልብስ ንፅህና፣ የምግብ ዝግጅትና የቤት አያያዝ የመሳሰሉ ተግባራትን ማድረግ፡፡
- ሕሙማንን መንከባከብ፣ የአእምሮ ጤና ህክምናና የሒሳብ አያያዝ የመሳሰሉ ሙያዊ ተግባራትን ማከናወን፡፡
3. ገንዘብ
- በአይነት (ቁሳቁስ) ወይም በገንዘብ (ብር) መርዳት
- ገንዘብ ሊያስገኙ በሚችሉ ተግባራት መሳተፍ
- ብር 495 ለአንድ ተጠቃሚ የሚያስፈልጉትን የምግብ፣ የአልባሳት እና የህክምና ወጪ ይሸፍናል
No comments:
Post a Comment